የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፈ።

ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጥቅምት 3 ቀን 2014 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ክቡር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው ካቶሊካውያን ካህናትን፣ ገዳማውያንን እና መላውን ምእመናንን በመወከል የመልካም ምኞት መግለጫ ልከውላቸዋል። በመግለጫውም ክቡርነታቸው በአስተዳደር ዘመናቸው ኢትዮጵያ ሕዝቦች በፍቅር፣ በአንድነት እና በሰላም የሚኖሩባት ሀገር እንድትሆን እንዲሁም ባህሏ ታሪኳ እና ሞራላዊ ልዕልናዋ ተጠብቆ እንድትኖር በሚያደርጉት ጥረት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ከጎናቸው የምትቆም መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሀገራችን ለሁሉም ልጆቿ እኩል ዕድል የምትሰጥ፣ ድሃ የማይበደልባት፣ ፍትሕ የማይጓደልባት እና የሰው ልጅ ክብር የሚጠበቅባት ትውልዱም በሞራል፣ በቅንነት እና በታማኝነት እሴቶች የሚገነባባት ሥርዓት እንደሚዘረጉ ተስፋ የምታደርግ መሆኑ ተገልጿል።

No photo description available.

Source: Ethiopian Catholic Secretariat