በደደቢት ፀሊሞ ግንባር ከጠላት ሰራዊት አባላት ጋር የተማረከው የጀነራል አበባው ታደሰ ሚስጥራዊ ደብዳቤ ዝርዝር ከዚህ በታች ማንበብ ይቻላል:: የፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ለሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች የተሰጡ ሚስጥራዊ ዶክመንቶች በጀግናው የትግራይ መከላከያ ሰራዊት እጅ ላይ ገብቷል:: የጀነራል አበባው ሚስጥራዊ ዶክመንት ዝርዝር:-

ቀን 04/13/2014 ዓ.ም

ከጀነራል አበባው

ለሌተናል ጀነራል መሰለ

ለሌተናል ጀነራል መሀመድ

ለሌተናል ጀነራል ደሳለኝ

ለሌተናል ጀነራል ብርሀኑ እና ለሁሉም ኮር አዛዦች

1ኛ) 7ኛ እዝ እና ምስራቅ እዝ ሰሜን ምዕራብ እዞች ዛሬ ሁሉን ዝግጅት አጠናቁ እና ነገ ወደ ማጥቃት እንጀምራለን:: ማጥቃቱም ትላንት የጀመርነውን ሁለቱን ሀይሎች የማገናኘት ስራ ይሆናል:: የመሬት: የጠላት: የወገን አሰላለፍ ጨርሱና አሳውቁኝ::

2ኛ) እነ መሰለ ዛሬ የጀመራቹትን በፍጥነት አጠናቁ::

ቀን 04/13/2014 ዓ.ም

ከሁመራ

ለሁሉም ኮር

አስተባባሪዎች ለሁሉም ሹፌሮች መኪና የያዙ ያለ ስራ የተቀመጡትን ወደ እዝ ትራንስፖርት እንድታስገቡና በጎደለበት ቦታ በጋራ እንዲያገለግሉ ላኳቸው::

ቀን 05/13/2014 ዓ.ም

ከ7ኛ እዝ

ለሁሉም ኮር አዛዦች

መስተካከል ያለባቸው ድክመቶች የሰው ሀይል እና የንብረት አስተዳደር ቁጥጥር እንዲሁም አመራር ክፍተት እንዳሉ የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ:: ተዋጊና ድጋፍ ሰጪ ስታፍ ላይም መንጠባጠብ እየታየ መሆኑ መረጋገጥ አለበት:: ክ/ጦር ከክፍሉ እየወጣ በየጫካውና ከኃላ ካለው ስታፍ ኮር ተቀላቅሎ ያለ የሰው ሀይል አለ:: አድራሻው የማይታወቅ የሰው ሀይል እንዳለም ሪፓርታችሁ ያመለክታል:: ይህ የሰው ሀይል አስተዳደር የቁጥጥር ችግር በፍጥነት መፈታት አለበት:: እኛ እየጠበቅን ካለንበት ሁኔታ አድራሻው የማይታወቅ የሰው ሀይል አለ ማለት ችግር እንዳለ ያመለክታል::

ከንብረት አስተዳደር እና ቁጥጥር አንፃርም በርካታ ችግሮች እየታዩ ነው:: ሬድዮዎች በብዛት እየጠፉ ነው:: ለጠፋ ሬድዮ ተጠያቂ አካል መኖር አለበት:: ሬድዮ ጥሎ የሚመጣ አመራር ላይ እርምጃ መውሰድ አለባችሁ:: እስካሁን ባደረግነው ውግያ እስከ ትላንት ድረስ ባለው 4,150 የሰራዊት አባላት መስዋዕት ሆኖ ተመዝግቧል::